ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳኑ ጄኔራል አኮል ኩር ኩች ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳኑ ጄኔራል አኮል ኩር ኩች ጋር ዛሬ ጠዋት ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸው በምስራቅ አፍሪካ መረጋጋትን እና ልማትን በማረጋገጥ የጋራ ግቦች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡