በኦሮሚያ ክልል በ7 ዞኖች በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮችን መምረጥ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጅማን ጨምሮ ከሰባት ዞኖች ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮችን መምረጥ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
በዚሁ መሠረትም÷ ከጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ እየተካሄደ መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም ተናግረዋል፡፡
እስካሁንም ከጅማ ዞን 10 ወረዳዎች ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ ተወካዮች ተመርጠዋል ብለዋል፡፡
በምክክሩ የሚሳተፉ አካላት አሳታፊነት ላይም በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡
በወርቃአፈራሁ ያለው