የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ 19 ጤና ጣቢያዎች የቀዶ ሕክምና የማዋለድ አገልግሎት እየሰጡ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

March 27, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ19 ጤና ጣቢያዎች የሚሰጠው የቀዶ ሕክምና የማዋለድ አገልግሎት የእናቶችና ሕጻናትን ጤና በመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው የእናቶችና ሕጻናት ጤና ዳይሬክተር ስንዱ መኩሪያ÷ የሕክምና አገልግሎቱ በሆስፒታሎች ላይ ያለውን ጫና ከመቀነስ ባሻገር የእናቶችና የሕጻናት ጤና በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ጤና ጣቢያዎችን በማዘመን ሆስፒታሎች የሚሰጡትን ሌሎች አገልግሎቶች ጤና ጣቢያዎች እንዲጀምሩ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡