የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

By Tibebu Kebede

June 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 775 የላብራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 156 ደርሷል፡፡