የሀገር ውስጥ ዜና

በአዳባ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Shambel Mihret

March 28, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ኤጀርሳ ቀበሌ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የምዕራብ አርሲ ዞን ትራፊክ ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ከማል አማን እንዳሉት፤ አደጋው የደረሰው ከጉብሳ ወደ አዳባ እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ከባድ ተሽከርካሪ ፍሬን በጥሶ በመገልበጡ ነው።

በአደጋው ሹፌሩ፣ ረዳቱን እና ከላይ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል።

በሁለት ሰዎች ላይም ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ሃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በመላኩ ገድፍ