የሀገር ውስጥ ዜና

በመላ ሀገሪቱ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ

By Feven Bishaw

March 28, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ከቀኑ 9 ሠዓት 46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

ሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል የተቋረጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል።

የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

እስከዛ ድረስም ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ተቋሙ ጠይቋል፡፡