Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ ኬሪያ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤነታቸው መልቀቃቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ገለፁ፡፡

ወይዘሮ ኬሪያ በመቐለ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤዎች ሀላፊነታቸውን በመልቀቅ ለተተኪው አፈጉባኤ ሲያስረክቡ የቆዩት መልቀቂያቸውን ለምክር ቤቱ በማቅረብ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ወይዘሮ ኬሪያ ሚያዚያ ወር 2010 ዓመተ ምህረት ላይ ነበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው የተመረጡት፡፡

ምክር ቤቱ 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን የፊታችን ረቡዕ እና ሀሙስ ለማካሄድ አባላቱን ጠርቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.