የሀገር ውስጥ ዜና

አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በኡጋንዳ የቀድሞ አፈ-ጉባኤ መታሰቢያ መርሐግብር ላይ ተሳተፉ

By Feven Bishaw

March 29, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በኢንቴቤ በተከበረው የቀድሞ የዩጋንዳ አፈ-ጉባኤ ጃኮብ ኦላንያ መታሰቢያ የሽልማት መርሐግብር ላይ ታድመዋል፡፡

አፈ-ጉባኤ ታገሰ በወጣቶች ላይ ባተኮረው የመታሰቢያ መርሐግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የአፍሪካ ወጣቶች በአፍሪካዊ እሴቶች እና ማንነት አንፆ መቅረፅ ይገባል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡