አንጋፋዋ አርቲስት እናኑ ደጉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በባህል ቡድን ውስጥ ለረጅም ዓመታት ያገለገለችው አንጋፋዋ አርቲስት እናኑ ደጉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች፡፡
አርቲስቷ በተለይም÷ በፉከራ፣ ሽለላና ቀረርቶ ሥራዎቿ በሕዝብ ዘንድ ትታወቃለች፡፡
የአርቲስቷ ሥርዓተ-ቀብርም ዛሬ ከቀኑ 8 ሠዓት በሰሚት ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን እንደሚፈጸም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡