Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ” የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ” በሚል መሪ ሐሳብ ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው እና በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት የተዘጋጁትን የመማሪያ መጽሐፍት ለሁሉም ተማሪዎች ለማዳረስ ያለመ የንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በመርሀ ግብሩም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለአንድ ወር የሚቆየው ይህ መጽሐፍ የማሰባሰብና የመለገስ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ስብራትን ለመጠገን እኔም ድርሻ አለኝ በሚል ሀሳብ ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋጾኦ እንዲያበረክት ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘመቻውን ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች በንቃት በመሳተፍ በክልሉ ያጋጠመውን የመፅሐፍ እጥረት በማቃለል እንደ ሀገር የገጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙም ጠይቀዋል።

በትምህርት የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተሟላ የትምህርት ግብዓት ማቅረብ እንደሚገባ ገልጸው፤ አመራሩ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ አለበት ብለዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማሕበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ለትምህርት ተደራሽነት ከሚደረገው ርብርብ ባሻገር ለትምህርት ጥራት ትልቅ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመለስ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.