Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የአርሶ አደሮች በዓል መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የመጀመሪያ ዙር የአርሶ አደሮች በዓል መካሄድ ጀምሯል፡፡

በበዓሉ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች፣ ከዞኖችና ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ከወረዳዎች የተውጣጡ አካላት ተገኝተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ለልማት አጋዦችና ሞዴል የልማት አርበኞች እውቅና እና ሽልማት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

በዓሉን የክልሉ የእርሻ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ እንዳዘጋጀው የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.