ቢዝነስ

የተመድ የልማት ትብብር የአፍሪካ ዳይሬክተር የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

April 01, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥታቱ ድርጅት የልማት ትብብር የአፍሪካ ዳይሬክተር ያኩብ አል ሂሎ እና የድርጅቱ ረዳት ጸሐፊና አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር) የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽኑ እያከናወናቸው የሚገኙ ኢንቨስትመንት ተኮር ሥራዎችን እና ፓርኩ ያለበትን ወቅታዊ የኦፕሬሽን እንቅስቃሴ አብራርተዋል፡፡

ያኩብ አል ሂሎ በበኩላቸው÷ በፓርኩ የተመለከቱትን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በማድነቅ ለወጣት ሴቶች የተፈጠረው ሰፊ የሥራ ዕድል አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መክረዋል፡፡