የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ለውጡን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ

By Amele Demsew

April 02, 2024

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ከተሞች ‘ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን” በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነዉ፡፡

በዞኑ የድጋፍ ሰልፉን እያደረጉ ያሉ ተሳታፊዎች የለውጡን ስኬቶች የሚመለከቱ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ለለውጡ አመራር ድጋፍ ማሳየታቸውን የዘገበው ኦቢኤን ነው፡፡