የሀገር ውስጥ ዜና

በሙከ ጡሪ ከተማ ለውጡን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ

By Meseret Awoke

April 02, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ሙከ ጡሪ ከተማ ለውጡን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ባለፋት ዓመታት በለውጡ የመጡትን የማህበራዊ፣ ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ውጤቶችን ለመደገፍ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የወል ትርክት ለጠንካራ ሀገረመንግስት ግንባታ መሰረት ነው! ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም! በምክክርና መደማመጥ ሰላምን እናጸናለን! ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን! ድላችንን እንጠብቃለን ለቀጣይ ስኬት በጋራ እንሰራለን! ቃል በተግባር! ፈተና ብልጽግናችንን ከማረጋገጥ አይገታንም! የሚሉና ሌሎች ሀገራዊ አንድነትን የሚያጸኑ መፈክሮችን ሰልፈኞቹ አሰምተዋል።