Fana: At a Speed of Life!

የህዝቡ መልዕክት የብልፅግና ጉዞ በጠንካራ መሰረት ላይ እየተገነባ መሆኑን ያረጋግጣል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝቡ ያስተላለፈው መልዕክት የሚያረጋግጠው የብልፅግና ጉዞ በጠንካራ መሰረት ላይ እየተገነባ መሆኑን እንሚያሳይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ የተካሄደውን ህዝባዊ ሰልፍ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ህዝቡ ጠንካራ ሀገርና መንግስት እንዲኖረው ትግል አድርጓል ብለዋል፡፡

አትዮጵያ የሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ሀገር መሆኗን በመግለጽ፤ በህብረብሔራዊ አንድነት የብሔር ብሔረሰቦች መብት የተከበረባት ሀገር እንደምትገነባ ገልጸዋል።

ብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት የሚፈለገውን ግብ ለማሳካት በሳል አመራር እንደሚሰጥ ጠቅሰው፤ የክልሉ ህዝብ ለውጡን በመደገፍ በመስዋዕትነት የተገኘውን ድል እንደሚጠብቅም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ከለውጥ ጀምሮ የህዝቡን ድል ለመጠበቅ እና የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

ዝናብና በረዶ ቢዘንብም በመላው ኦሮሚያ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ ለመረጠው መንግስት ያለውን ድጋፍ በማሳየት የበለጠ እንድንሰራ አበረታቶናልም ነው ያሉት፡፡

ከተገኘው ለውጥ ጎን በመቆም የብልፅግና ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ የክልሉን ፀጥታ ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች ሀገራዊ ለውጡ ያመጣውን ውጤት የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ‘ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን” በሚል መሪ ሀሳብ ባካሄዱት የድጋፍ ሰልፍ የለውጡን ስኬቶች የሚመለከቱ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ለለውጡ አመራር ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል።

ሰልፈኞቹ ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ የወል አቅማችንን በማጎልበት ኢኮኖሚያችንን በጽኑ መሰረት ላይ እንገነባለን! ህብረብሔራዊነታችንን በማጠናከር ለሁሉም የምትመች ሀገር እንገነባለን! የሚሉና ሌሎች ሀገራዊ አንድነትን የሚያጸኑ መፈክሮችን በማሰማት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.