Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክሮች ሀገራዊ ችግሮችን የመፍታት አቅም አላቸው – የጃፓን አምባሳደር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካኝነት የሚካሔዱ ውይይቶች ሀገራዊ ችግሮችን የመፍታት አቅም እንዳላቸው በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ አመላከቱ፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ከአምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ያከናወናቸውን ሥራዎች እና ወደ ፊትም ስለሚሠሩ ተግባራት እንዲሁም ኮሚሽኑ አሁን ስላለበት ሁኔታ ዋና ኮሚሽነሩ አብራርተዋል፡፡

አምባሳደር ሺባታ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ገለጻ አመሥግነው፤ ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አድንቀዋል፡፡

በኮሚሽኑ አማካኝነት የሚካሔዱ አሳታፊ እና የጋራ ውይይቶችም ሀገራዊ ችግሮችን የመፍታት አቅም እንዳላቸው እምነታቸውን መግለጻቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመልክቷል።

ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራዎች ስኬትም ጃፓን የምታደረገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.