ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ ሉዋንዳ የሚያደርገውን በረራ ወደ ዕለታዊ አሳደገ

By ዮሐንስ ደርበው

April 03, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ከሣምንታዊ ወደ ዕለታዊ ማሳደጉን አስታውቋል፡፡

የበረራው ወደ ዕለታዊ ማደግም ለመንገደኞች የተመቸ የጉዞ አማራጭ እንዲኖራቸው ያስችላል ብሏል አየር መንገዱ፡፡

ወደ አንጎላ እየተደረገ ያለው በረራ አራት አስርት ዓመታትን ማስቆጠሩን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡