Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ ተገብቷል – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ የተደራጀ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ፥ ህዝብ ምላሽ ሊሰጥባቸው ይገባል በሚል የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ተለይተዋል።

በዚህም የሰላም፣ የኑሮ ውድነት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ህገወጥ የማዕድን ንግድን የመሳሰሉት ጉዳዮች ምላሽ እንዲሰጥባቸው ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች መሆናቸውን አቶ አሻድሊ አመልክተዋል።

በመሆኑም ጥያቄዎቹን በመለየትና በማደራጀት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደተግባር መገባቱን ገልጸው ፥ ህዝቡን ያሳተፉ ዘላቂ የሰላም ግንባታ ስራዎች ትኩረት ያገኛሉ ብለዋል።

በተለይም የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደህብረተሰቡ የተቀላቀሉትን መልሶ የማደራጀት ተግባር በትኩረት እንደሚከናወን ተናግረዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.