Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ያሉ የቱሪስት መስህቦችን በጸረ ተህዋሲ የማስረጨት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ያሉ የቱሪስት መስህቦችን በጸረ ተህዋሲ ማስረጨት ስራ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀመረ።

የጸረ ተህዋሲያን ርጭቱ በብሔራዊ ሙዚየም ነው የተጀመረው፤ በሙዚየሙ ውስጥ ከተደረገው ርጭት ባለፈ በቅርሶች ላይም ርጭቱ ተከናውኗል።

ቱሪስቶች የጸረ ተህዋስ ርጭት የተደረገባቸውን ቅርሶች እንዲያውቁም መረጨታቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደሚለጠፍባቸው ተነግሯል።

በቀጣይም የጸረ ተህዋሲ ርጭቱ በጥያ ትክል ድንጋይ፣ በሀረር ግንብ፣ በጎንደር ፋሲለደስ እና በላሊበላ እያለ ሁሉንም ቅርሶች እንደሚያዳርስ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ጸረ ተህዋስ ርጭቱ በድህረ ኮቪድ-19 ወቅት ቱሪስቶች ዳግም ወደ ጉብኝት ሲመለሱ ያለ ስጋት ጉብኝታቸውን እንዲያከናውኑ ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል።

ከሰሞኑ ፎርብስ መጽሄት በድህረ ኮቪድ-19 ወቅት ይጎበኛሉ በሚል ቅድሚያ ግምት ተሰጥቷቸዋል ብሎ ካሰፈራቸው ውስጥ ኢትዮጵያ ትገኝበታለች።

በፍሬህይወት ሰፊው

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.