የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው

By Mikias Ayele

April 04, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ መክፈት የሚያስችል ስምምነት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት  አቶ ኢያሱ ወሰን መፈራረማቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ነው፡፡