የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፍቼ ጨምበላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Mikias Ayele

April 05, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጨምበላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው፤ በዓሉ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን አጠናክረን በጋራ በመቆም የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዳግም ቃል የምንገባበት እንዲሆንልን እመኛለሁ ብለዋል፡፡

በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡