የሀገር ውስጥ ዜና

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ የቤት አቅርቦት ችግርን መፍታት ያስችላል – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

By Meseret Awoke

April 06, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ያስችላል ሲሉ የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለፁ፡፡

የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ተደራሽ በማድረግ በኩል የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ በጋራ ግንዛቤ የሚኖረው ተግባራዊነት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የተገኙት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት ፥ መንግስት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማሟላት የቤት ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡

ከዚህ ባሻገርም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ከቤት አቅርቦት አኳያ ያለውን ችግር እንደሚፈታ ነው የገለጹት፡፡

በተለያዩ ጥናቶች መሠረት በኢትዮጵያ ዜጎች ከሚያገኙት ገቢ 80 በመቶ ድረስ ለቤት ኪራይ እንደሚያወጡ የተጠቀሰ ሲሆን ፥ የኪራይ ዋጋን እና የአቅርቦት ችግሩን ለመፍታት አዋጁ ሚናው የጎላ እንደሆነም አንስተዋል።

አዋጁ አከራይ እና ተከራይን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ተጠቃሚ እንደሚያደርግም አስገንዝበዋል፡፡

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና በክልል ተጠሪ ከተሞች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

በሜሮን ሙሉጌታ