የሀገር ውስጥ ዜና

በድሬዳዋ ከተማ የውኃ ጉድጓድ ሲቆፍሩ የነበሩ 2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Amele Demsew

April 06, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውኃ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ሕይወት ማለፉን የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አደጋው ዛሬ ከቀኑ 8 ሠዓት ተኩል አካባቢ በድሬዳዋ 03 ቀበሌ ደምሴ ረታ ሕንጻ ግሪን ዴይ ፔኒሲዮን ግቢ ውስጥ መከሰቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የውኃ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ የነበሩ የ45 ዓመት ጎልማሳ ለሥራቸው እንዲመቻቸው ብለው ያሰሩት ገመድ በድንገት በመፈታቱ ዘጠኝ ሜትር ጥልቀት ወዳለው ጉድጓድ ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን የአሥተዳደሩ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

የወደቁትን ግለሰብ ሕይወት ለማትረፍ በማሰብ ወደ ጉድጓድ የገቡት በቁፋሮ ሥራ ሲያግዙ የነበሩ የ40 ዓመት ግለሰብም በዚያው ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡