ስፓርት

በፓሪስ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

By Feven Bishaw

April 07, 2024

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በፓሪስ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንድም በሴትም አሸንፈዋል፡፡

መስታወት ፍቅር 02:20፡ 45 በመግባት የሴቶቹን ውድድር ስታሸንፍ በተመሳሳይ በወንዶች ሙሉጌታ ኡማ 02፡05፡33 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አሸንፏል፡፡

አትሌት እናት ጥሩ ሰው በ02፡20፡47በሴቶች ሁለተኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቅቃለች፡፡