ስፓርት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን አሸነፈ

By Shambel Mihret

April 07, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

ዛሬ 10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ለሀድያ ሆሳዕና ዳዋ ሁጤሳ 45+6′ ደቂቃ እንዲሁም ብሩክ ማርቆስ በ84ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያላዳነውን ብቸኛ ጎል በ17ኛው ደቂቃ ላይ ዮሴፍ ታረቀኝ አስቆጥሯል።