Fana: At a Speed of Life!

በለውጡ የተገኙ ድሎችን ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በለውጡ መንግሥት ያገኛቸውን ድሎች ለማስቀጠል ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል፡፡

በሲዳማ ክልል የሃዋሳ ከተማ እና የሰሜን ሲዳማ ዞን ነዋሪዎች በሃዋሳ ከተማ “ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን!” በሚል መሪ ሃሳብ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ፥ የሲዳማ ክልል በለውጡ መንግሥት ያገኛቸውን በርካታ ድሎች ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ዘመን ያለፈባቸውን አመለካከቶች በማንገብ የለውጡን ግስጋሴ ለማደናቀፍ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ፍፁም ተቀባይነት እንደሌላቸውም አንስተዋል፡፡

በሰልፉም ለውጡ ያስመዘገባቸውን በርካታ ውጤቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል ህዝቡ ከለውጡ መንግሥት እና መሪ ጎን መቆሙን አስመስክሯል ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የሲዳማ ህዝብ እኩልነቱን እና ነፃነቱን የተጎናፀፈው በለውጡ መንግሥት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ ለውጡን ለማስቀጠል ህዝቡ ሁሌም ድጋፉን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.