Fana: At a Speed of Life!

በዓሉ ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም እንዲከበር አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት አድርጊያለሁ – ኮሚሽኑ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኢድ-አልፈጥር በዓል ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም እንዲከበር አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን በመጠቆም በተለያዩ አማራጮች የጥንቃቄ መልዕክቶችን እያስተላለፈ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ስለሆነም በዓሉ ከአደጋ ክስተት ተጠብቆ እንዲከበር እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ኮሚሽኑ አስስቧል፡፡

ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ወይም 011-1-55-53-00፣011-1-56-86-01 ቁጥሮች ፈጥነዉ እንዲያሳውቁ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.