Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ900 በላይ ስታርት አፖች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ በሣይንስ ሙዚየም ተከፈተ።

ለሦስት ሣምንታት በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ የመጀመሪያ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ደረጃን የተሻገሩ እና ወደገበያ የመቀላቀል ደረጃ ላይ የደረሱ ስታርት አፖች  ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል።

የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃያት ካሚል፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ዐውደ-ርዩ የተከፈተው፡፡

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.