የሀገር ውስጥ ዜና

በአምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ ልዑክ በሳዑዲ ማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጎበኘ

By Mikias Ayele

April 08, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ ልዑክ በሳዑዲ ዓረቢያ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ጎብኝቷል፡፡

ጉብኝቱ ከሳዑዲ መንግስት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመገምገምና ለቴክኒክ ኮሚቴው ግብዓት ለመሰብስብ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ጉብኝቱ  ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ሒደት ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ተመላሾችን ለመለየት እንደሚያስችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሒደቱን በይፋ ማስጀመር የሚቻልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ያለመ መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡