ሕዝበ ሙስሊሙ የመረዳዳት ባህሉን እንደሚያስቀጥል እምነቴ ነው- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ሙስሊሙ እንደወትሮው ሁሉ በነገው በዓልም የአብሮነትና የመረዳዳትባህሉን እንደሚያስቀጥል እምነቴ የፀና ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡
ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ ለ1ሺህ 445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም÷ የሐይማኖቶች ሁሉ አስኳል ሐሳብ የሆነውን የአብሮነት፣ የመረዳዳት፣ የመከባበርና የመደጋገፍ ትዕዛዝና ባህል እንደወትሮው ሁሉ ሕዝበ ሙስሊሙ በነገው በዓልም እንደሚያስቀጥለው አምናለሁ ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ሕዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች ወንድምና እህት ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ለሀገር ብልጽግና፣ ሠላምና ለተሻለ ነገ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡