Fana: At a Speed of Life!

በረመዳን ወር የታየው አብሮነት ሊጠናከር ይገባል – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዒድ አል-ፈጥር በዓል ሲከበር የእምነቱ ተከታዮች በየአካባቢያቸው የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ለሚከበረው 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልእክታቸውም÷ የዒድ አል-ፈጥር በዓል የአብሮነት፣ የሰላምና የደስታ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በረመዳን ወር ወቅት ከተቸገሩ እና አቅም ከሌላቸው ወገኖች ጋር ጸሎትና ኢፍጣር በማድረግ የታየው አብሮነት መጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የእምነቱ ተከታዮች የዒድ አል-ፈጥርን በዓል በሚያከብሩበት ወቅት በየአካባቢያቸው የሚገኙ የተቸገሩ ወገኖችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማቅረብ እና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የሰላም፣ የደስታ፣ የአብሮነት እና ከፈጣሪ በረከት የሚገኝበት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሙስሊሙ ማኅበረሰብ የዒድ በዓልን ሲያከብር በረመዳን የጾም ወቅት ያሳየውን መረዳዳት በማጠናከር በመተዛዘን፣ በመደጋገፍና የተቸገሩ ወገኖች በማገዝ ሊሆን ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.