የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ ከድር ጁሀር የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Feven Bishaw

April 09, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር 1 ሺህ 445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸው ÷በዘንድሮው የረመዳን ወር በድሬዳዋ ህብረተሰብ ውስጥ የኖረው የፍቅር እና አብሮነት ውብ እሴት፥ በይበልጥ ደምቆ መታየቱን ነው የገለፁት፡፡

“የኢድ ዕለትም በረመዳን የጾም ወር የፈፀምናቸውን የአንድነት፥ የእዝነት፥ የመረዳዳት እና ሌሎች በርካታ መልካም እሴቶች አጠንክረን፥ በቀጣይ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ለማስቀጠል ለራሳችን ቃል የምንገባበት ልዩ ቀን ናት” ሲሉም ገልፀዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖችም በዓሉ የፍቅር፥ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡