ዩናይትድ ኪንግደም ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚገቡ የአበባ ምርቶች ላይ የምታስከፈለውን ቀረጥ ላልተወሰነ ጊዜ አነሳች
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ወደ ሀገሪቱ በሚገቡ የአበባ ምርቶች ላይ የምታስከፍለውን ቀረጥ ማንሳቷን አስታውቃለች፡፡
ውሳኔው ኢትዮጵያን ጨምሮ አበባ አምራች ለሆኑት የቀጣናው ሀገራት እና ሌሎች ሀገራት ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር ያላቸውን የንግድ ልውውጥ ቀላል እና ምቹ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
በውሳኔው መሰረትም አበባ አምራች የሆኑት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በዜሮ ታሪፍ ያተገደበ የአበባ ምርታቸውን ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ማስገባት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ይህም ሶስተኛ ሀገራትን እንደ መጓጓዣ ተጠቅመው ወደዩናይትድ ኪንግደም አበባ ለሚልኩ ሀገራት ትልቅ እድልን የፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ቀደም ሲል ከኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የሚላኩ የአበባ ምርቶች ላይ የ8 በመቶ ታሪፍ ያስክፍል እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
የታሪፍ እገዳው ከአሁን ጀምሮ ለሁለት አመታት ያህል የሚቆይ መሆኑን ተመላክቷል፡፡