የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ለሚሳተፉ የቻይና ባለሀብቶች ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

By Mikias Ayele

April 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከግንቦት 1 እስከ 5 በሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ለሚሳተፉ የቻይና ባለሀብቶች ትብብርለማድረግ የሚያስችል ምክክር ተካሂዷል፡፡

በቤጅንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች አስተባባሪ ኮሚቴ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ በኢትዮጵያ ቅድሚያ በሚሰጥባቸው ኢንቨስትመንት መስኮች በተለይም በንግድ እና በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ዕምቅ ዕድሎችን ለማስተዋወቅ የሚረዱ ፎረሞችን በጋራ በተለያዩ ከተሞች ለማዘጋጀት የሚያስችል ምክክር ተደርጓል።

በተጨማሪም ከግንቦት 1 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ በሚካሄደው  ኢትዮጵያ ታምርት ኤክፖና ባዛር ላይ የቻይና ባለሀብቶች በንቃት እንዲሳተፉ በጋራ ለማስተባበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በኢትዮጵያ የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት የሚያደርጉ ልዑካን ቡድኖችን በጋራ ለማስተባበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን ከቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡