የሀገር ውስጥ ዜና

የፀጥታ ችግር የነበሩባቸው አካባቢዎች ከስጋት ወጥተው ፊታቸውን ወደ ልማት አዙረዋል – አቶ አሻድሊ ሀሰን

By Mikias Ayele

April 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ችግር የነበሩባቸው አካባቢዎች ከስጋት ወጥተው ፊታቸውን ወደ ልማት ማዞር ችለዋል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለፁ፡፡

የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ባለፉት ስምንት ወራት በፀጥታ ዘርፍ የተከናወኑ መደበኛ እና ወቅታዊ ተግባራትን ገመግሟል፡፡

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት÷ በተሠራው የተቀናጀ የፀጥታ ስራ የህዝቡን ሠላም እና ደህንነት ማስጠበቅ ተችሏል።

የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር በመሆን የሚያበረታታ ተግባር ማከናወኑን ጠቅሰው÷ በክልሉ የፀጥታ ችግር የነበሩባቸው አካባቢዎች ከስጋት ወጥተው ፊታቸውን ወደ ልማት ማዞር መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ አሁን የተገኘውን ሠላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሁሉም የፀጥታ መዋቅር ሁሉን አቀፍ ስራዎቹን በመስራት ህዝቡ በሠላም ወጥቶ እንዲገባ የጋራ ጥረትን ይጠይቃል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡