Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

በዛሬው ዕለት እየተመረቁ ያሉ ተማሪዎች 778 ሲሆኑ÷ ከዚህ ውስጥ 26 በሶስተኛ ዲግሪ፣ 350 በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

402ቱ ደግሞ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በህክምና፣ በጥርስ ህክምና፣ በላብራቶሪ በኢንቫይሮሜታል ነርሲንግ፣ ሚድዋይፈሪ እና በፊዚዬቴራቢ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት ራስገዝ ከሚሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ጅማ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው።

ለዚህም ዩኒቨርሲቲው የገቢ አቅምን ማሳደግን ጨምሮ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል በቅርቡ የተሰጠውን የብሔራዊ መውጫ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 379 የዩኒቨርሲቲው ጤና ኢንስቲትዩት የህክምና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

በአትክልት በቀለ እና ወርቅአፈራው ያለው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.