Fana: At a Speed of Life!

የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች የአረጋውያን ማቆያና የሕፃናት ሕክምና ማዕከላትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች በአዲስ አበባ የተመረጡ የአረጋውያን ማቆያ እና የህፃናት ሕክምና ማዕከላትን ጎብኝተዋል።

በመርሃ-ግብሩ የጉባዔው የበላይ ጠባቂ አባቶች የኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ጎብኝተዋል።

በመርሃ-ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌልና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

የኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ብርሃን ተድላ፤ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለመጡ የልብ ችግር ላለባቸው ህፃናት ነፃ የልብ ሕክምና እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የሕክምና አገልግሎቱ ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በወረፋቸው መሠረት ለሚመጡ የሚቀርብ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም የህፃናትን ሕይወት እየታደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የልብ ማኅበር ፕሬዝዳንት እንዳለ ገብሬ፤ 16 ሺህ ሰዎች የልብ ቀዶ ጥገና ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል በልብ ሕክምና ረገድ እያደረገ ላለው ስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሃ-ግብሩ የጉባዔው የበላይ ጠባቂዎች የሕክምና አሰጣጡን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.