Fana: At a Speed of Life!

በሴቶችና የህጻናት ጥቃት ዙሪያ 94 መዝገቦች በምርመራ ላይ ሲሆኑ፤ 4 መዝገቦች የፍርድ ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል- ወ/ሮ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለውን የሴቶች እና የህጻናት ጥቃት ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መገምገማቸውን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
 
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለውን የሴቶች እና የህጻናት ጥቃትን በተመለከተ ዛሬ የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣ ከጠቅላይ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ አዲስ አበባ ፖሊስ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ጋር በመሆን ግምገማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
 
በግምገማውም፣ “ከኮቪድ 19 መከላከል ስራ ጋር ተያይዞ በቤት መቆየት ምክንያት እና የፍትህ መስሪያ ቤቶች ተዘግተዋል በሚል ጥቃቶች መጨመራቸውን፣ ወደ ፍትህ አካላት መጠቆም መቀነሳችውን እና መረጃ አያያዝ ክፍተቶችን በዝርዝር ተነጋግረንበታል” ብለዋል።
 
ሆኖም 94 መዝገቦች በፖሊስ ምርመራ ላይ መሆናቸውን እና 23 ክሶች መመስረታቸውን እንዲሁም በዚሁ ጊዜ ውስጥ በአራት መዝገቦች ላይ የፍርድ ውሳኔ መሰጠታቸውንም አረጋግጠዋል።
 
“በፍርድ ቤት በኩልም የሴቶች እና ህጻናት ችሎቶች በሙሉ አቅማችው እንዲሰሩ መከፈታቸውን አይተናል” ሲሉም አስታውቅዋል።
 
“አሁንም ቢሆን ብዙ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸዉም ተረድተናል” ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች “በተለይ የግንዛቤና የመከላከል ስራ የሁሉም አካል ስራ መሆኑን መገንዝብ ያሻል” ብለዋል።
 
ወደፊትም ችግሩን ለመግታት በሚሰራው ስራ መረጃ እና አሰራራን በመናበብ እንዲሁም ቅንጅት የሞላበት መሆን እንዳለበት መግባባት ላይ መድረሳቸውንም አስታውቅዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.