የሀገር ውስጥ ዜና

569 የሸኔ አባላት እጃቸውን ሰጡ

By Melaku Gedif

April 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን 569 የሽብር ቡድኑ ሸኔ አባላት መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን ሰጡ፡፡

የሽብር ቡድኑ አባላት በሕዝብ ላይ ሲያደርሱት በነበረው ዘርፈ ብዙ በደል ተጸጽተው በሰላም እጃቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ባደረሱት በደል ህዝብ እና መንግስትን ይቅርታ የጠየቁት አባላቱ ÷ ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ሌሎች የሸኔ አባላትም መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል እጃቸውን እንዲሰጡ መምከራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡