ስፓርት

የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በደሴ ከተማ ተካሄደ

By Meseret Awoke

April 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በደሴ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመጪው ሐምሌ ወር የሚካሄደውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ ሀገራዊ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራት ንቅናቄ መጀመሩ ይታወቃል።

ዛሬ በደሴ ከተማ በተደረገው ችቦ ማብራትና ቅብብሎሽ መርሐ- ግብር የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር የቴክኒክና ህዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ ቢልልኝ መቆያ ፥ በውድድሩ ኢትዮጵያ የተሻለ ውጤት እንድታስመዘገብ ከወዲሁ የቅደመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚሁ የንቅናቄ ስነ- ስርዓት የፌዴራል፣ የክልል፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲና የደሴ ከተማ አመራር አባላትና የስፖርት ቤተሰቦች መገኘታቸውም ነው የተነገረው።

በስነ -ስርዓቱ ማጠናቀቂያም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከአማራ ክልል የኦሎምፒክ ችቦ ተረክቧል።

በወርቅነህ ጋሻሁን