የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 71 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Meseret Awoke

April 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስት ዙር በተከናወነ በሳውዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 71 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 71 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ፥ ዘጠኙ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል።

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡