Jeremy Doku of Manchester City celebrates after scoring a goal to make it 4-1 in the Premier League match between Manchester City and Luton Town at the Etihad Stadium, Manchester, England. Saturday 13th April 2024. (Photo by Lexy Ilsley/Manchester City FC)

ስፓርት

ማንቸስትር ሲቲና ኒውካስል ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ማንቸስተር ዩናይትድ አቻ ተለያይቷል

By Melaku Gedif

April 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማንቸስትር ሲቲና ኒውካስል ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት ሲያሸንፉ ማንቸስተር ዩናይትድ አቻ ተለያይቷል፡፡

ሉተን ተዎንን በሜዳው ያስተናገደው ማንቸስትር ሲቲ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ኒውካስል ዩናይትድ በበኩሉ ቶተንሃም ሆትስፐርን 4 ለ 0 ረትቷል፡፡

በተመሳሳይ ብሬንት ፎርድ ሼፍልድ ዩናይትድን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ በርንሌይ እና ብራይተን ደግሞ 1 ለ 1 ተለያይተዋል፡፡

በሌላ በኩል ኖቲንግሃም ፎረስት እና ዎልቨር ሀምፕተን 2 ለ 2 እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትድ እና በርንማውዝ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡