የሀገር ውስጥ ዜና

ከ10 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድ ጥገና ሥራ ተከናወነ

By ዮሐንስ ደርበው

April 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በ10 ቢሊየን 356 ሚሊየን 19 ሺህ 307 ብር የወቅታዊና መደበኛ የመንገድ ጥገና ሥራ መከናወኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

ለጥገና ሥራው አገልግሎት ላይ ዋለው ገንዘብም ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ለመንገዶች ጥገናና የመንገድ ደኅንነት ማስፈጸሚያ የተሰበሰበ የመንገድ ፈንድ ገቢ መሆኑን የአሥተዳደሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

መንገዶች እንዳይጎዱ ተገቢውን ጥገና እንዲያገኙ የማድረጉ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡