የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል በ250 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ውሃ ፋብሪካ ተመረቀ

By Amele Demsew

April 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በ250 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ውሃ ፋብሪካ ዛሬ ተመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢንድሪስ አብዱን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፋብሪካው 200 ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ እድል መፍጠሩንም መረጃው ጠቁሟል።