የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል በበልግ ወቅት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ይለማል ተባለ

By Shambel Mihret

April 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ የበልግ ወቅት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች የማልማት ሥራ መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹና ሌሎች የክልሉ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የዘንድሮ የበልግ እርሻ ሥራ በባሌ ዞን ሲናና ወረዳ ተጀምሯል።

አቶ ጌቱ ገመቹ በወቅቱ፣ በዘንድሮው የበልግ እርሻ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች የማልማት ሥራ እየተካሄደ ነው ብለዋል።

ልማቱ ሜካናይዜሽንን ጨምሮ ሌሎች የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ እየተካሄደ መሆኑን አክለዋል።

የዘንድሮ የበልግ አዝመራ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግም ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን እንደተናገሩ ኢዜአ ዘግቧል።