የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ከአለም ምግብ ፕሮግራም ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋር መከሩ

By Amele Demsew

April 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ከአለም ምግብ ፕሮግራም ምክትል ዋና ዳይሬክተር ካርል ሳኩ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እየተሰሩ ላሉ የልማት እና የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች የአለም ምግብ ፕሮግራም ያለውን አጋርነት እና ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።