የሀገር ውስጥ ዜና

ከአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ለኢትዮጵያ ሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ630 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰበሰበ

By Amele Demsew

April 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ለኢትዮጵያ ሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ630 ሚሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ አስታወቁ፡፡

የገንዘብ ማሰባሰቢያ ኮንፍረንሱን ኢትዮጵያ ፣ብሪታኒያ እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ያዘጋጁት መሆኑንም ነው አምባሳደር ታዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የገለፁት፡፡

በኮንፍረንሱ የኢትዮጵያ መንግስት ቀዳሚ ትኩረት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል፣ የአደጋ ስጋት ቅነሳና ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም መሆኑን ለኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች ማስገንዘባቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡