የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኦርዲን በድሪ የሸዋል ዒድ በዓል አብሮነትን በሚያጎላ መልኩ እንዲከበር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

By Tamrat Bishaw

April 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የሸዋል ዒድ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ አብሮነትንና ፍቅርን በሚያጎላ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዎ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በክልሉ በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የሸዋል ዒድ በዓል ከመቼውም በላይ በታላቅ ድምቀት እና ስኬት መጠናቀቁን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ለበዓሉ ስኬት ሚና የነበራቸውን የክልሉ ህዝብ፣ የፀጥታ እና ህግ አስከባሪ አካላት፣ የአጎራባች ክልሎች ልኡካን እንዲሁም ሌሎች አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በክልሉ ህዝብና መንግስት ስም ምስጋና ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።