ዓለምአቀፋዊ ዜና

የኬንያ መከላከያ ሃይል ዋና አዛዥ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ

By Meseret Awoke

April 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ መከላከያ ሃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦጎላ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡

የኬኒያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አደጋውን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸውን የኬኒያ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም በኬኒያ የሦስት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ከነገ ጀምሮ አውጀዋል፡፡

የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በጄኔራሉ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡