የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የብክለት መከላከል ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

April 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብክለት መከላከል ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡

የንቅናቄ መድረኩ ‘ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ’ በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች አበቤ÷ ከተማዋን ውብ እና ምቹ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ተናግረው፤ አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉት የኮሪደር ልማት ሥራዎች በቀጣይ ለሚጠበቀው ውጤት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል።

ከተለያዩ የብክለት ምንጮች ከተማዋን ለመጠበቅ በሚሰራው ሥራ ሁሉም አካል ተሣታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሰሎሞን ይታየው እና ምንተሥኖት ሙሉጌታ